Fana: At a Speed of Life!

ዶናልድ ትራምፕ በቀረቡባቸው ክሶች ላይ መስክረውብኛል ያሏቸውን ከፍተኛ ባለስልጣናት አባረሩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቀረቡባቸው ክሶች ላይ መስክረውብኛል ያሏቸውን ሁለት ከፍተኛ ባለስልጣናት አባረሩ።

ትራምፕ ስልጣናቸውን ያለ አግባብ በመጠቀምና የምክር ቤቱን ስራ በማደናቀፍ ክስ ቀርቦባቸው ጉዳያቸው በምክር ቤት ከታየ በኋላ ነጻ መባላቸው ይታወሳል።

ፕሬዚዳንቱ በዚህ ሂደት ምስክር በመሆን ስሜን አጥፍተዋል ያሏቸውን ሁለት ከፍተኛ ባለስልጣናት ከስራ አሰናብተዋል።

በዚህም በአውሮፓ ህብረት የአሜሪካ አምባሳደር ጎርደን ሰንድላንድ እና በፀጥታው ምክር ቤት የዩክሬንን ጉዳይ የሚከታተሉትን ሌተናል ኮሎኔል አሌክሳንድር ቪንድማንም ከኋይት ሀውስ እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጥተዋቸዋል ነው የተባለው።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከቀረቡባቸው ክሶች ነፃ ከሆኑ ወዲህ ሰራተኞችቸው እንዲነቃቁ እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.