Fana: At a Speed of Life!

ዶክተር ፍጹም አሰፋ ከተመድ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 24 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት እና የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ኃላፊዎች ጋር በአገር-አቀፍ የማገገሚያ የልማት ፕሮግራሞች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የተመድ የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት ማስተባበሪያ ኃላፊ ዶክተር ካትሪን ሱዚ እና የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት የኢትዮጵያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ቱርሀን ሳሌ ተገኝተዋል፡፡

በውይይቱ መንግስት ከጦርነቱ በኋላ ስለሚያከናውነው “ማንም ወደኋላ የማይቀርበት” አገር-አቀፍ የማገገሚያ ተግባር ዕቅድ ዝግጅት በስፋት ምክክር ተደርጓል።

በዚህ ወቅትም የማገገሚያ መርሀ-ግብሩ በጤናው፣ በትምሀርት፣ በስራ ፈጠራ፣ በመልካም አስተዳደር፣ በሰላም ግንባታ እንዲሁም ሌሎች የልማት ዘርፎችን በማካተት ሁሉን አቀፍ በሚሆንበት አግባብ ላይ መምከራቸውን ሚኒስቴሩ ለጣቢያችን የካለው መረጃ ያመላክታል።

የማገገሚያ የልማት ፕሮግራም ዕቅዱ በመንግስት መሪነት የሚዘጋጅ ሲሆን በትግበራ ላይ ካለው የአስር አመት የልማት ፕሮግራም ዕቅድ ጋር ተጣጥሞ የሚሄድ እና የልማት አጋሮችን በጋራ የሚያስተባበር መሆኑ ተመላክቷል።

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.