Fana: At a Speed of Life!

ጊኒያውያን ለፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ድምጽ እየሰጡ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጊኒያውያን ለፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ድምጻቸውን እየሰጡ ነው።

በምርጫው የ82 አመቱ ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ ለሶስተኛ ጊዜ ሃገራቸውን ለመምራት እየተወዳደሩ ነው።

ፕሬዚዳንቱ ለሶስተኛ ጊዜ ለመወዳደር ሕገ መንግስቱን ማሻሻላቸው ይታወሳል፤ በርካቶች ይህን አካሄድ ቢተቹትም እርሳቸው ግን መወዳደሩን መርጠዋል።

ሴሉ ዳሊያን ዲያሎ ደግሞ የአልፋ ኮንዴ ዋነኛ ተፎካካሪ ሆነው በምርጫው ቀርበዋል።

5 ነጥብ 4 ሚሊየን ሰዎችም ለመምረጥ የተመዘገቡ ሲሆን፥ አጠቃላይ የምርጫው ውጤት ቀናት ሊወስድ ይችላል ተብሏል።

ምርጫውን ለማሸነፍ አንደኛው ዕጩ ከ50 በመቶ በላይ ድምጽ ማግኘት ይጠበቅበታል።

የአሁኑ ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ በፈረንጆቹ 2010 በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በማሸነፍ ሃገሪቱን እየመሩ ይገኛል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.