Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በመሆን የባቱ ዱግዳ የመስኖ ልማት ፕሮጀክትን መረቁ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 26 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በመሆን የባቱ ዱግዳ የመስኖ ልማት ፕሮጀክትን መርቀዋል።

በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እንዲሁም የቀድሞው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተገኝተዋል።

የመስኖ ፕሮጀክቱ በአሁኑ ጊዜ 2 ሺህ ሔክታር መሬት የማልማት አቅም ያለው ሲሆን፣ በአካባቢው የሚገኝ ተጓዳኝ የመስኖ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ደግሞ 15 ሺህ ሔክታር መሬት ማልማት እንደሚችል ተገልጿል።

ሁለቱ መሪዎች ከምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ቀደም ብለው በኦሮሚያ ክልል ዱግዳ ወረዳ የሚገኝ የችግኝ ጣቢያ መጎብኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.