Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ በመካከለኛው ምስራቅ ከተወጣጡ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ተወካዮች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በመካከለኛው ምስራቅ ከተወጣጡ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ተወካዮች ጋር ተወያዩ ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ለሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች አቡዳቢ መግባታቸው ይታወቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቡዳቢ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼህ አብደላ ቢን ዛይድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በአሁኑ ስዓትም ከ250 በላይ ከሚሆኑ በመካከለኛው ምስራቅ ከተወጣጡ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ተወካዮች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ፣ በየሚኖሩባቸው ሀገራት የአምልኮ ስፍራዎች እና ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችሉ ቦታዎችን ማግኘት በሚችሉባቸው መንገዶች ዙሪያ መክረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከላይ በተጠቀሱት እና በሌሎች ማህበራዊ ጉዳዮች እና ተግዳሮቶች ዙሪያ ለቀረቡ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በኣላዛር ታደለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.