Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ባይደን የመሣሪያ ቁጥጥር ሥምምነቱ በአስቸኳይ እንዲተገበር አሳሰቡ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የመሣሪያ ቁጥጥር ሥምምነት ማዕቀፉ በአስቸኳይ እንዲተገበር አሳሰቡ፡፡

የአሜሪካ ምክር ቤት ሴናተሮች በቀረበው የመሣሪያ ቁጥጥር ማዕቀፍ ላይ ተስማምተዋል።

ይህን ተከትሎም ፕሬዚዳንቱ ሕግ አውጪዎች የመሣሪያ ቁጥጥር ማሻሻያውን በፍጥነት ወደ ነጩ ቤተ መንግስት እንዲልኩ ማዘዛቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሳምንት የመሣሪያ ቁጥጥር ረቂቅ ደንብን በአብልጫ ድምፅ ማሳለፉ የሚታወስ ነው።

ረቂቁ ሰዎች መሣሪያ መግዛት የሚችሉበትን ዕድሜ ከ18 ወደ 21 ከፍ እንዲል ይደነግጋል።

መሣሪያ እንዲገዛ ዕድሜው የሚፈቅድለት ማንኛውም ሰው ከ15 ተተኳሽ ጥይቶች በላይ የሚይዝ የጥይት መጋዘን መግዛት እንደማይችልም በወጣው ደንብ ተደንግጓል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.