Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያግዙ ግብዓቶችን ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የሰላም ሚኒስቴር ለዘጠኙ ክልሎች፣ ለሁለቱ ከተማ አስተዳደሮችና ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ተወካዮች የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያግዙ ግብዓቶችን ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉን የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር እንዳሸው ጣሰው፣ እንዲሁም የክልሎችና የከተማ አስተዳደር ኮሚሽነሮች በተገኙበት  አስረክበዋል።

ሚኒስቴሩ ከተለያዩ ድርጅቶች የገዛቸውንና በድጋፍ ያገኛቸውን 68 ሺህ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎች፣ 5 ሺህ 750 ጓንቶች፣ 1ሺህ 600 ሊትር ሳኒታይዘር፣ 63 ኢንፍራሬድ የሰውነት ሙቀት መለኪያ እና በድንበር አካባቢ በለይቶ ማቆያ ማእከሎች እየሰሩ ለሚገኙ የፀጥታ አካላት የሚሆን ለሶስት ክልሎች 45 ሙሉ ልብስ ዩኒፎርሞችን ድጋፍ አድርጓል።

በዚሁ ወቅት የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እንደተናገሩት÷ የኮሮና ወረርሽን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ልክ እንደ ህክምና ባለሙያዎች ሁሉ ወረርሽኙን ከፊት ሆነው ለሚጋፈጡት የፀጥታ አካላት ድጋፍና ዕገዛ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

ግዕባቶቹን የተረከቡት የክልሎችና የከተማ አስተዳደር ኮሚሽነሮች እና የፌዴራል ፖሊስ በበኩላቸው÷ የሰላም ሚኒስቴር ላደረገልን ድጋፍና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከጎናችን መቆሙን ስላሳየን ምስጋናችን ትልቅ ነው ማለታቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘኘው መረጃ ያመለክታል ።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.