Fana: At a Speed of Life!

ሚድሮክ ኢትዮጵያ ግሩፕ 5 ሊትሩን የምግብ ዘይት በ330 ብር ለሸማቶች ማቅረብ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሚድሮክ ኢትዮጵያ ግሩፕ የምግብ ዘይት በተመጣጣኝ ዋጋ በአዲስ አበባ ከተማ እያቀረበ ይገኛል።

ግሩፑ መንግስት በምግብ ዘይት ላይ የጣለውን ታክስና ቀረጥ በማንሳቱ 5 ሊትሩን የምግብ ዘይት በ330 ብር ለሸማቶች እያቀረበ እንደሚገኝ ነው የተገለፀው።

ሚድሮክ ኢትዮጵያ ግሩፕ የንግድ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር በቀለ ጎላዶ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት፤ መንግስት የሸማቶችን የኑሮ ጫና በመጋራት ታክስ እና ቀረጥ በማንሳቱና ሚድሮክም በአነስተኛ የትርፍ እዳግ የምግብ ዘይቱን አቅርቧል።

አሁን ላይ የምግብ ዘይቱን በአዲስ አበባ በሚገኙት አራት ኪዊንስ ሱፐርማርኬት ለተጠቃሚዎችም እየቀረበ መሆኑን ተናግረዋል።

ወደ ሃገር ውስጥ የገባው የምግብ ዘይት ለሸማቶች ተደራሽ እንዲሆንም አንድ ሸማች ከሁለት ባለአምስት ሊትር ዘይት በላይ መግዛት እንዳይችል ተደረጓል ነው ያሉት ዶክተር በቀለ ጎላዶ።

በቀጣይ ምርቱን በሃገር ውስጥ ለማምረት እየተገነባ የሚገኘው ፋብሪካ እስኪጠናቀቅ ድረስ ግን የምግብ ዘይት ምርቱ ሳይቆራረጥ እንዲቀርብም ይደረጋል ብለዋል ።

በፍሬህይወት ሰፊው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.