Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ከቻይና ጋር ያላት ግንኙነት ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ ማደጉን ፕሬዚዳንት ፑቲን ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያዉ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሀገራቸዉ ከቻይና ጋር ያላት የሁለትዮሽ ግንኙነት ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ማደጉ እንዳስደሰታቸው ገለፁ።
ፕሬዚዳንት ፑቲን ሀገራቸዉ ባዘጋጀችው የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ በቪዲዮ ኮንፍረንስ ባስተላለፉት መልዕክት፥ በአለም አቀፍ መድረክ አገራቱ አንዱ የሌላውን ጥቅም በጠበቀ እና ባከበረ መልኩ ግንኙነታቸውን መገንባታቸውን አንስተዋል።
ፑቲን ቻይና በኢኮኖሚ እያደገች መሆኗን በመግለጽ ይህም ሊገታ የማይችል ተፈጥሯዊ ሂደት ነው ብለዋል።
አክለውም በቻይና ላይ የሚጣሉ ገደቦች እና ማዕቀቦች ፍትሃዊ እንዳልሆኑ እና የአለም አቀፍ ህግና ደንቦችንም እንደሚቃረኑ ገልፀዋል።
በወታደራዊ ዘርፍም ቻይና ራሷን የመከላከል መብት እንዳላት ነዉ የተናግሩት።
ሞስኮ ይህንን እንደ ስጋት አትመለከተውም ያሉት ፕሬዚዳንቱ፥ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ለአለም መረጋጋት ትልቅ አስተዋፅዖ አለውም ብለዋል።
በቻይና እና በሩሲያ በተፈጠረዉ እጅግ መልካም የሆነ ግንኙነት ረክተናል፣ የበለጠ ጥልቅ፣ ትርጉም ያለው እና ለሀገራቱ ህዝቦች አዎንታዊ ተጽእኖ ሊያመጣ ይችላል ብለን እናስባለን ማለታቸዉን ዥንዋን ዋቤ አድርጎ ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
በአመለወርቅ ደምሰው
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.