Fana: At a Speed of Life!

ሩስያ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን ከመስከረም ወር ጀምሮ በስፋት ልታሰራጭ መሆኑን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 25፣ 2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) ሩስያ የኮሮና ቫይረስ ክትባትን ከመስከረም ወር ጀምሮ በስፋት ለማሰራጨት ማቀዷን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስትር ሚኻኤል ሙራሽኮ አስታወቁ።

ሩስያ ከ25 ሚሊየን በላይ የዓለም ህዝብ ላጠቃው የኮሮና ቫይረስ ክትባት ማግኘቷን በቅርቡ ይፋ ማድረጓ ይታወሳል።

ይህንንም ተከትሎ የጤና ሚኒስትሩ በመጀመሪያ ዙር የሚከተቡት የጤና ባለሙያዎችና መምህራን መሆናቸውን ተናግረዋል።

ክትባቱም ሙሉ ለሙሉ በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ መሆኑንም አንስተዋል።

የጤና ሚኒስትሩ የክትባት ምርት እየተከናወነ ጎን ለጎን ደግሞ ፈዋሽነቱ እየተፈተሸ ነው ብለዋል።

እስከ አሁን ለሦስተኛ ደረጃ ሙከራ ከተመዘገቡ 40 ሺህ በጎ ፈቃደኞች መካከል 2 ሺህ 500 ሰዎች መመረጣቸውንም አስታውቀዋል።

በአንጻሩ ምዕራባውያን የክትባቱ ፈዋሽነት ላይ የተዓማኒነት ጥያቄ ያነሱ ሲሆን፦ ሩስያ በበኩሏ ጥያቄውን ውድቅ አድርገዋለች።

በተጨማሪም ሩስያ ከ20 ሀገራት በላይ 1 ቢሊየን መጠን የያዘ ስፑትኒክ ቪ ክትባት እንዲመረትላቸው ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጸዋል።

ሆኖም ግን የዓለም ጤና ድርጅት በክትባቱ ዙሪያ ከሩሲያ ባለስልጣናት ጋር እየተነጋገረ መሆኑንም በትናንትናው እለት ማስታወቁ አይዘነጋም።

የዓለም ጤና ድርጅት አዲሱን የሩሲያ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ለመመዘንም ከሀገሪቱ በቂ መረጃ እንዳላገኘም ነው በመነገር ላይ የሚገኘው።

ምንጭ፦ ሞስኮታይምስ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.