Fana: At a Speed of Life!

በሃይቲው ፕሬዝዳንት ግድያ ላይ የኮሎምቢያና የአሜሪካ ቅጥር ነብሰ ገዳዮች እጅ አለበት ተባለ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በሀይቲው ፕሬዝዳንት ጆቬኔል ሞይስ ግድያ 28 አባላትን የያዘ የአሜሪካዊያን እና ኮሎምቢያዊያን ገዳዮች ቡድን ተጠያቂ እንደሆነ የሃሪቱ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የሃይቲ ፖሊስ ኃላፊ ሊዮን ቻርለስ እንደገለፀው፣ ከገዳዮቹ ቡድን አባላት ውስጥ 26ቱ የኮሎምቢያ ዜግነት ያላቸው ሲሆኑ የተቀሩት 2ቱ ደግሞ አሜሪካውያን ናቸው፡፡

አሁን እየወጡ ያሉ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት፣ ከፕሬዝዳንቱ ግድያ ጋር በተገናኘ 15 ኮሎምቢያዊያን እና 2 በሃይቲ ነዋሪ የሆኑ አሜሪካውያን ገዳዮች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ 4 ኮሎምቢያዊያን ተጠርጣሪዎች ደግሞ ከፖሊስ ጋር በነበረ የተኩስ ልውውጥ እንደተገደሉ ታውቋል፡፡ 7ቱ ተጠርጣሪዎች እስካሁን መሰወራቸው የሃሪቱ ፖሊስ መረጃ ያሳያል፡፡

በሌላ በኩል ከኮሎምቢያ መከላከያ ሚኒስቴር የወጣው መረጃ እንደሚጠቁመው ከገዳዮቹ ውስጥ 6ቱ በጡረታ የተገለሉ የቀድሞ የኮሎምቢያ ወታደሮች መሆናቸውን ነው፡፡

በተያያዘ ዜና፣ የፕሬዝዳንት ሞይስ መገደል እና የባለቤታቸው ማርቲን መቁሰል ከተሰማ በኋላም 2 ሰዎች ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ሀሳብ ማቅረባቸውም ነው የታወቀው፡፡

ምንጭ፡ አልጀዚራ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.