Fana: At a Speed of Life!

በሊባኖስ ቤሩት ከፍተኛ የፍንዳታ አደጋ መድረሱ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሊባኖሷ ቤሩት ከተማ ከፍተኛ የፍንዳታ አደጋ መድረሱ ተነግሯል።

ከስፍራው የወጡ ሪፖርቶች እንዳመላከቱት ፍንዳታው በከተማዋ ወደብ አቅራቢያ በሚገኙ መጋዘኖች አካባቢ ማጋጠሙን ነው።

ለፍንዳታው ምክንያቱ ምን እንደሆነ እስካሁን የተገለፀ ነገር የለም።

ፍንዳታው ከተሰማ በኋላ በማህበራዊ ትስስር ድረ ገፆች ላይ የተጫኑ ተንቀሳቃሽ ምስሎች ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ህንጻዎችን እና ጭስ አስመልክተዋል።

በፍንዳታው የደረሰው የጉዳት መጠን እስካሁን እንዳልተጣራ የተገለፀ ሲሆን፥ በትንሹ 78 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ነው የተነገረው።

የሊባኖስ የጤና ሚኒስትር ሀማድ ሀሰን አደጋውን አስመልክቶ፥ በርካታ ጉዳቶች መድረሳቸውን እና የደረሰው ውድመትም ከፍተኛ መሆኑን አስታውቅዋል።

የሊባኖስ ብሄራዊ የዜና አገልግሎት በበኩሉ በአደጋው ስፍራ ነፍስ የማዳንና አደጋውን የመከላከል ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው ብሏል።

ፍንዳታው ያጋጠመው የከተማዋ ወደብ የሚገኝበት አቅራቢያ ሲሆን በስፍራው ተከማችቶ የነበረው አልሙኒያም ናይትሬት ከ6 ዓመታት በፊት ከአንድ መርከብ ላይ ወርዶ በስፍራው እንዲከማች ተደርጓል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.