Fana: At a Speed of Life!

በመላው ሀገሪቱ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ እና በገበያው እጥረት እንዲፈጠር የሰሩ ከ64 ሺህ በላይ ህገ ወጥ ነጋዴዎች እርምጃ ተወሰደባቸው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)በመላው ሀገሪቱ የኮቪድ 19 ወረርሽን ምክንያት አድርገው የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ እና በገበያው እጥረት እንዲፈጠር የሰሩ ከ64 ሺህ በላይ ህገ ወጥ ነጋዴዎች እርምጃ እንደተወሰደባቸው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል አስታወቁ።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ የነበራቸው ሚኒስትሩ ÷ሆን ብለው ገበያው እንዳይረጋጋ እና እጥረት ለመፍጠር ሲሰሩ የነበሩ የሸማች ማህበራት አመራሮችን ጨምሮ ህገ ወጥ ነጋዴዎች ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ብለዋል።

በተለይ የመሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ዋጋ በመጨመር የተሳተፉ ከ2 ሺህ 100 በላይ ነጋዴዎች ጉዳያቸው በህግ የተያዘ ሲሆን 460 የሚሆኑት ደግሞ ፍርድ ተሰቶባቸውል ነው ያሉት ።

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል በአጠቃላይም በመላው ሀገሪቱ ከ64 ሺህ 900 በላይ ህገ ወጥ ነጋዴዎች የተለያዩ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ሲሉ ገልፀዋል ።

ሰሞኑን በዘይት ላይ የተስተዋለው ጭማሪ አቅራቢ ሀገራት በሆኑት ኢንዶኖዚያ እና ሲንጋፖር በገጠመ የኮቪድ ተጽእኖ ነው መሆኑን ያነሱት ሚኒስትሩ፤ በቀጣይ ቀናት ወደነበረበት ዋጋም ይመለሳል ነው ያሉት ።

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በገበያው ላይ የሚፈጠሩ የዋጋ ጭማሪዎችን በቀጣይነትም ለመቆጣጠር የሸማቾችን የክምችት ሁኔታ በየእለቱ ይከታተላል ብለዋል።

በየክልሎች ያሉ መጋዘኖችም የምርት አያያዝና ስርጭታቸው ላይ ቁጥጥሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

በሀይለዮሱስ መኮንን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.