Fana: At a Speed of Life!

በትራምፕ የታጩት ኤሚ ኮኒ ባሬት የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ መሆናቸው ተረጋገጠ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የታጩት ኤሚ ኮኒ ባሬት የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ እንዲሆኑ በሴኔቱ ፀደቀላቸው።
የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሊካሄድ ሳምንት በቀረበት ወቅት ኤሚ ኮኒ ባሬት ከዘጠኞቹ አንዷ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው መመረጣቸው ለዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ ድል ነው ተብሏል።
ሪፐብሊካኖቹ 52 ለ48 በሆነ የድምፅ ብልጫ ከምርጫው በፊት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሹመት እንዳይፈፀም ከፍተኛ ተቃውሞ ሲያደርጉ የቆየቱትን ዴሞክራቶች በማሸነፍ ሹመቱ እንዲፀድቅ አድርገዋል።
የ48 ዓመቷ ኤሚ ኮኒ ባሬት ትናንት ምሽት ከዶናልድ ትራምፕ ጎን ሆነው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።
ሹመቱ በቀጣይ ዘመናት ወግ አጥባቂዎቹ በአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውስጥ 6 ለ 3 ብልጫ እንዲኖራቸው በማድረግ የሚፈልጉትን ውሳኔ በቀላሉ እንዲያሳልፉ
ያስችላቸዋል የሚል ግምት እንዲቀመጥ አድርጓል።
በሜይን ድጋሚ ለመመረጥ ከፍተኛ ትግል የሚጠብቃቸው ሴናተር ሱሳን ኮሊን የትራምፕ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሹመት የተቃወሙ ብቸኛዋ ሪፐብሊካን ናቸው።
ይህ የዶናልድ ትራምፕ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሹመት ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ በፈረንጆቹ 2017 ኔኢል ጎርሰችን እና በ2018 ብሬት ካቭኖ ቀጥሎ ሶስተኛዋ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.