Fana: At a Speed of Life!

አዳማና አምቦን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች የድጋፍ ሰልፎች ተካሄዱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  አዳማና አምቦን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች ለውጡን በመደገፍ ሰልፎች ተካሄዱ።

የአዳማ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ለውጡን በመደገፍ ዛሬ ከጧቱ 12 ሰዓት ጀምረው ነው ደማቅ የድጋፍ ሰልፍ ያካሄዱት ።

ሰልፈኞቹ “በትግላችን ያመጣነውን ለውጥ እንጠብቃለን እንከባከባለን ! ለለውጡ ውጤታማነት የድርሻችንን እንወጣለን ! ” የሚል መፈክር  በማሰማት ነው የድጋፍ ሰልፉን ያካሄዱት።

“መነሻችን መደመር መድረሻችን ደግሞ ብልፅግና ነው ! ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በመጠበቅ ለውጡን ከዳር እናደርሳለን !” የሚሉ መፈክሮችም ሰልፈኞቹ ከያዟቸው የሚጠቀሱ ናቸው ብሏል ኢዜአ በዘገባው ።

በምእራብ ሸዋ ዞን አምቦ ከተማም ለውጡን በመደገፍ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።

በዞኑ ከሚገኙ 22 ወረዳዎች የተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በድጋፍ ሰልፉ ላይ ተሳትፈዋል።

በተመሳሳይ የገላን ከተማ እና አካባቢው ነዋሪዎች በተመሳሳይ የድጋፍ ሰልፍ አካሂደዋል።

የአምቦ ሰልፍ ገፅታ

የአምቦ ሰልፍ ገፅታ

የአዳማ ሰልፍ ገፅታ

የባቱ ከተማ ሰልፍ ገፅታ

በአዳነች አበበ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.