Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ እና ኩዌት መካከል የሰራተኛ ስምምነት ለመፈራረም የሚያስችል ድርድር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ጥር 14፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ እና ኩዌት መካከል የሰራተኛ ስምምነት ለመፈራረም የሚያስችል ድርድር መካሄዱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ድርድሩ ላለፉት ሁለት ቀናት በኩዌት ሸራተን ሆቴል የተደረገ ሲሆን፥ በጥሩ ውጤት መጠናቀቁም ነው የተነገረው።

በዚህ ድርድር ያልተጠናቀቁ ጥቂት ጉዳዮች እና ነጥቦችን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ መስማማታቸውም ተገልጿል።

በድርድሩ በኢትዮጵያ በኩል አምባሳደር አብዱልፈታህ አብዱላሂ እና የኤምባሲው ዲፕሎማቶችን ጨምሮ በኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምሥራቅ ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ጂብሪል እንዲሁም ከሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተውጣጣ የልዑካን ቡድን መሳተፉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.