Fana: At a Speed of Life!

በዓለም ላይ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ20 ሚሊየን አለፈ

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዓለም ዙሪያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከ20 ሚሊየን ማለፉ ተገለፀ።

የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ በድረ ገጹ ያወጣው መረጃ እንዳመለከተው በዓለም ዙሪያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 20 ሚሊየን 90 ሺህ 541 ደርሷል።

እንደ ዩኒቨርሲቲው መረጃ በዓለም ላይ 12 ነጥብ 2 ሚሊየን ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ፤ 735 ሺህ ገደማ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል።

ከዚህም ውስጥ በአሜሪካ ብቻ 5 ሚሊየን 94 ሺህ 314 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው እና ከ163 ሺህ በላይ ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፥ ከዓለም ቀዳሚውን ስፍራ ይዛለች።

3 ሚሊየን 57 ሺህ 470 ዜጎቿ  በኮሮና ቫይረስ የተያዙባት ብራዚል ሁለተኛ ስፍራን ስትይዝ፤ ከ2 ሚሊየን 268 ሺህ በላይ ዜጎቿ በቫይረሱ የተያዙባት ህንድ ሶስተኛ ስፍራ ላይ ተቀምጣለች።

890 ሺህ 799 ዜጎቿ  የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሩሲያ ደግሞ አራተኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ፤ 563 ሺህ 595 ዜጎቿ በቫይረሱ የተያዙባት አፍሪዊቷ ሀገር ደቡብ አፍሪካ በዓለም አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.