Fana: At a Speed of Life!

በ40 ሚሊየን ብር ወጪ የመዲናዋን የመንገድ ዳር መብራቶች ለማዘመን እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከ40 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመዲናዋን የመንገድ ዳር መብራቶች መልሶ የመጠገንና የማስጌጥ ስራዎች እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ በተለያየ ምክንያት የተበላሹ የመንገድ ዳር የመብራት ምሰሶዎችን በአዲስ የመተካት፣ የመብራት መስመሮችን የመቀየር፣ የመንገድ ዳር መብራቶችን የመጠገንና የማስጌጥ ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

ባለስልጣኑ እስከ ጥር ወር መጨረሻ ድረስ 3 ሺህ 44 የመንገድ ዳር የመብራት ምሰሶዎች ጥገና እንዲሁም 2 ሺህ 175 አምፖሎችን የመቀየር ስራ መስራቱን አስታውቋል።

ለመንገድ ዳር መብራቶቹ የተደረገው ጥገና በምሽት ያለውን የተሽከርካሪ እና የሰው እንቅስቃሴ ሰላማዊ እና ምቹ እንዲሆን አስችሏልም ነው ያለው ባለስልጣኑ።

የመንገድ ዳር መብራቶች ለረጅም ጊዜ አገልግሎት እንዲሰጡም ህብረተሰቡ አስፈላጊውን እንክብካቤና ጥበቃ እንዲያደርግ ጥሪ መቅረቡን ከአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.