Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 6 ወራት 435 ኪ.ሜ የመንገድ ግንባታና የጥገና ስራዎች መከናወናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 6 ወራት 435 ኪ.ሜ የመንገድ ግንባታና የጥገና ስራዎች መከናወናቸውን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ባለስልጣኑ በግማሽ ዓመት ልዩ ልዩ የግንባታና የጥገና ስራዎች 435 ኪ.ሜ በማከናወን የእቅዱን 88 በመቶ ማሳካቱን ገልጿል፡፡

ባለስልጣኑ ላለፉት ስድስት ወራት ካከናወናቸው አጠቃላይ የ74 ኪ.ሜ አዳዲስ የመንገድ የግንባታ ስራዎች መካከል 13 ኪ.ሜ የአስፋልት ፣15.7 ኪ.ሜ የጠጠር፣7.6 ኪ.ሜ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውስጥ ለውስጥ መንገዶች፣15 ነጥብ 1 ኪ.ሜ የኮብል ፣22 ኪ.ሜ የእግረኛ መንገዶች መልሶ ግንባታ፣ 0 ነጥብ 5 ኪ.ሜ የድሬኔጅ መስመር እና 0 ነጥብ 14 ኪ.ሜ የድጋፍ ግንብ ስራዎች ይገኙበታል፡፡

በተጨማሪም 34 ነጥብ 1 ኪ.ሜ የአስፋልት፣18 ነጥብ 3 ኪ.ሜ የጠጠር፣ 303 ኪ.ሜ የድሬኔጅ መስመር ፅዳትና ጥገና፣ 5 ነጥብ 6 ኪ.ሜ. የእግረኛ መንገድ በድምሩ በ6 ወራት ውስጥ 361 ኪ.ሜ የጥገና ስራዎች ማከናወን መቻሉን ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

በተያያዘም የሽሮ ሜዳ – ቁስቋም ክፍል አንድ መንገድ ፕሮጀክት የአስፋልት ማልበስ ስራ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑን ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.