Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምታደርገውን ያልተገባ ጫና የሚቃወም ሰልፍ በሚኒሶታ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 21 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምታደርገውን ያልተገባ ጫና እና ጣልቃ ገብነት የሚቃወም ሰልፍ በሚኒሶታ ግዛት ተካሄዷል።

በሰልፉ ላይ በሚኔሶታ ግዛት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ-ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ተሳታፊ ሆነዋል።

ሰልፉ የተዘጋጀው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዛሬ በሚኒሶታ ግዛት ዳኮታ ካውንቲ ቴክኒካል ኮሌጅ የሚያደርጉትን የስራ ጉብኝት ተከትሎ ነው።

ሰልፈኞቹ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ይገኙበታል ተብሎ በሚጠበቀው ቴክኒካል ኮሌጅ በማቅናት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

በዚህም የባይደን አስተዳዳር በኢትዮጵያ ላይ የሚከተለውን የተሳሳተ ፖሊሲና አድሏዊ አቋም እንደማይቀበሉና አካሄዱን እንዲያስተካከል መልዕክት ማስተላለፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በሚኒሶታ ግዛት እየተካሄደ ያለው ሰላማዊ ሰልፍ የ”በቃ” ወይም ‘#NoMore’ ዘመቻ አካል ነው።

ሚኒሶታ በአሜሪካ በርካታ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ከሚኖርባቸው ግዛቶች በዋንኛነት የምትጠቀስ ናት።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.