Fana: At a Speed of Life!

አርመንያ እና አዘርባጃን የደረሱትን የተኩስ አቁም እንዲያከብሩ ተመድ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አርመንያ እና አዘርባጃን የደረሱትን የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያከብሩ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ዋና ፀሃፊው በናጎሮኖ ካራባህ ግጭት በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት አውግዘዋል፡፡

እስካሁን ድረስ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ከደረሰው ጥቃት አንዱ የሆነውንና ቅዳሜ በተፈጸመ ጥቃት ህፃናትን ጨምሮ የ13 ሰዎች ህይወት ያለፈበትን ክስተት አንስተዋል፡፡

አርመንያ እና አዘርባጃን የናጎሮኖ ካራባህ ግዛት የይገባኛል ግጭት ውስጥ ከገቡ የሰነባበቱ ሲሆን፤ በዚህ የተነሳ በሁለቱም ወገኖች ሰላማዊ ዜጎች ህይወት እያለፈ ይገኛል፡፡

የናጎርኖ-ካራባህ ክልል መከላከያ ሚኒስቴር በተደረገው ውጊያ 710 የሚደርሱ ወታደሮች ህይወት ማለፉን አስታውቋል፡፡

ከፈረንጆቹ 1990ዎቹ ጀምሮ በአካባቢው በተነሳው ግጭት ሳቢያ ወደ 30 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ይነገራል፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.