Fana: At a Speed of Life!

አዲሱ ዴልታ ‘ፕላስ’ የኮቪድ-19 ዝርያ በከፍተኛ ፍጥነት የመዛመት አቅም አለው-ጥናት

አዲስ አበባ፣ጥቅምት13፣2014 (ኤፍ ቢሲ) አዲሱ  ዴልታ ‘ፕላስ’  የተሰኘው የኮቪድ-19 ዝርያ በከፍተኛ ፍጥነት የመዛመትአቅም እንዳለው ጥናት አመላክቷል፡፡

በብሪታኒያ  የሚገኙ ተመራማሪዎች በአዲስ መልክ እራሱን የቀየረው ዴልታ ‘ፕላስ’ የኮሮረና ቫይረስ ዝርያ ከሌሎቹ በፈጠነ መንገድ ከሰዎች ወደ ሰዎች የመተላለፍ አቅም እንዳለው ገልጸዋል።

የብሪታኒያ ጤና ደኅንነት ኤጀንሲም አዲሱን ቫይረስ “ምርምር ከሚደረግባቸው የኮቪድ-19 ዝርያዎች” ዝርዝር ውስጥ ያስገባው ሲሆን÷ ይህም ምን ያህል አስጊ እንደሆነ ያሳያል ተብሏል።

በተጨማሪም ተመራማሪዎችዴልታ ፕላስ የተሰኘው አዲስ የቫይረስ በአሁኑ ወቅት ጥቅም ላይ እየዋሉ ባሉ የክትባት አይነቶች መከላከል እንደሚቻል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ቫይረሱ ከዴልታ ጋር ሲነጻጸርም የስርጭት መጠኑ ከፍተኛ መሆን ነው የብሪታኒያ ጤና ደኅንነት ኤጀንሲ ያስታወቀው፡፡

እስካሁን በተደረጉ ጥናቶች መሰረት በመላው ዓለም በሺህዎች የሚቆጠሩ የኮቪድ-19 የቫይረስ ዝርያዎች መኖራቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.