Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በ6ኛው ፓወሪንግ አፍሪካ ጉባኤ ላይ ተሳተፈች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ በ6ኛው ፓወሪንግ አፍሪካ ጉባኤ ላይ ተሳትፋለች።

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከአሜሪካው ኤግዚም ባንክና ከዓለም ባንክ አመራሮች፣ ከአሜሪካ የንግድ ምክር ቤት አባላት፣ ከአሜሪካ የፋይናንስ ልማት ኮርፖሬሽን እና ከሌሎች የልማት ድርጅት አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።

በተጨማሪም በዋሽንግተን ከሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ጋር በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይም ውይይት አድርገዋል።

ከዚህ ባለፈም የህዳሴ ግድብ ያለበትን ደረጃ እና ከዲፕሎማቲክ ማህበረሰቡ በሚያስፈልጉ ድጋፎች ዙሪያ መወያየታቸውንም ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላቱ ግድቡ ተጠናቆ ኃይል ማመንጨት እስከሚጀምር ድረስ ከመንግስት ጎን በመሆን በሁሉም ዘርፍ ድጋፋቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ውይይታቸው በኢትዮጵያ በኃይል አቅርቦት እና ማመንጫ ኢንቨስትመንቶች፣ በስፔስ ልማት ፕሮግራሞች እና በሌሎችም ዘርፎች አብሮ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር ተብሏል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.