Fana: At a Speed of Life!

ኢንጅነር ታከለ ኡማ ሁለት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 19 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ ሁለት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ።

ኢንጅነር ታከለ የጎተራ ቄራ ፑሽኪን አደባባይ እና የወሎ ሰፈር ዑራኤል የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶችን ነው የጎበኙት።

የመንገድ ፕሮጀክቶቹ 5 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸው ሲሆን፥ ከቻይና መንግስት በተገኘ ድጋፍ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጪ የሚገነቡ ናቸው።

የፑሽኪን አደባባይ ጎተራ ማሳለጫ የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታ መስከረም ወር መጨረሻ ላይ የተጀመረ ሲሆን፥ በሁለት አመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

የመንገድ ፕሮጀክቱ አሁን ላይ የዲዛይን ስራው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ የዋሻ ስራ ቁፋሮው ተጀምሯል።

ይህ መንገድ ሲጠናቀቅ ከፑሽኪን እና ጎተራ መንገዶች ጋር በመመጋገብ በአካባቢው ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ ይቀርፋል ተብሏል።

የወሎ ሰፈር ዑራኤል የመንገድ ፕሮጀክት ግንባታን በዚህ አመት ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑም ተገልጿል።

በሃይማኖት ኢያሱ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.