Fana: At a Speed of Life!

የዶ/ር ኢሌኒን መግለጫ በጽኑ እንቃወማለን- ዘመዴነህ ንጋቱ

አዲስ አበባ፣ህዳር 17፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የብሉስፔስ ባለድርሻ የሆነችው እሌኒ ገብረመድህን በማህበራዊ ትስስት ገጾች በሰፊው በተሰራጨው ቪዲዮ ላይ ያደረገችውን ንግግር በጽኑ እንደሚቃወሙ የኢኮኖሚ ባለሙያው ዘመዴነህ ንጋቱ ገለጹ።
የኢኮኖሚ ባለሙያው ዘመዴነህ ንጋቱ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፥ የብሉስፔስ ድርጅት ባለአክሲዮናችን የሆነችው እሌኒ ገ/መደህን የኢትዮጵያን መንግስት አስመልክታ ያደረገችው ንግግር በጣም አስደንግጦኛል፤ አሳዝኖኛልም ብለዋል።
አምስታችንም ባለአክሲዮኖች በተሰራጨው የቪዲዮ መግለጫ በፅኑ የምናወግዝ መሆኑን እንገልፃለን ብለዋል ባለሙያዉ።
አክለውም በህዝብ ከተመረጠው የኢትዮጵያ መንግስት ጎን ሙሉ በሙሉ (100%) እንቆማለን ሲሉም በቲዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.