Fana: At a Speed of Life!

እነ አቶ ጃዋር መሀመድ ዳኛው ይነሳልን ሲሉ አቤቱታ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 4፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በእነ ጃዋር መሀመድ መዝገብ ላይ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን ማሰማት ጀምሮ የነበረ ቢሆንም እነ አቶ ጃዋር ዳኛው ከመዝገባችን ይነሳልን ሲሉ አቤቱታ አቅርበዋል፡፡

ችሎቱ በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በልደታ አዳራሽ መስማት ተጀምሮ ነበር።

ይሁን እንጅ እነ አቶ ጃዋር ዳኛው ጉዳያችንን ገለልተኛ ሆኖ ላይመለከትልን ስለሚችል ከመዝገባችን ላይ ይነሳልን ሲሉ ባለ 7 ገጽ አቤቱታ አቅርበዋል፡፡

ፍርድ ቤቱም አቤቱታውን ተመልክቶ ዳኛው መዝገቡ እንዲመረመርና በመዝገቡ ላይ ትዕዛዝ እስከሚሰጥበት ድረስ ተጠርጣሪዎቹ በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲቆዩ እና መጥሪያ ሲደርሳቸው የሚመጡ ይሆናል በማለት ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

መዝገቡም ወደ መዝገብ ቤት እንዲመለስ አዟል፡፡

ከዚህ በፊት የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በዚህ መዝገብ ላይ በአጠቃላይ በተጠርጣሪዎች ላይ የሚመሰክሩ 5 ምስክሮች ከመጋረጃ በስተጀርባ የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ሲል አቤቱታ ማቅረቡ ይታወሳል።

ፍርድ ቤቱም አምስቱ የዐቃቤ ህግ ምስክሮች ከመጋረጃ በስተጀርባ ቃላቸውን እንዲሰጡ ብይን መስጠቱ የሚታወስ ነው።

በታሪክ አዱኛ

ተያያዥ ዜናዎችን ያንብቡ

የኦፌኮ አመራራር አቶ በቀለ ገርባና አቶ ጃዋር መሃመድ ፍርድ ቤት ቀረቡ
መርማሪ ፖሊስ በአቶ ጃዋር መሃመድ ቤት በግለሰብ እጅ የማይገኙ ሳተላይቶችና ከውጭ በድብቅ የገቡ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ማግኘቱን ገለጸ
ፍርድ ቤቱ አቶ ጃዋርና አቶ በቀለን ጨምሮ 14 ተጠርጣሪዎች ላይ አቃቤ ህግ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን እንዲያሰማ ብይን ሰጠ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.