Fana: At a Speed of Life!

ካማላ ሃሪስ በአሜሪካ ታሪክ ዕጩ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡ ሶስተኛዋ ሴት ሆነዋል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካ ዕጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ካማላ ሃሪስን ዕጩ ምክትል ፕሬዚዳንት አድርገው መምረጣቸውን ትናትና ምሽት አስታውቀዋል።

በጆ ባይደን ምክትል ዕጩ ፕሬዚዳንት በመሆን የተመረጡት ካማል ሃሪስ ለዚህ ሚና የመጀመሪያዋ የጥቁር እና የእስያ የዘር ሀረግ ያላቸው መሆን ችለዋል።

በሌላ በኩል በሀገሪቱ ታሪክ ለአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንትነት በዕጩነት የቀረቡ ሶስተኛዋ ሴት መሆናቸውም ነው የተነገረው።

የካሊፎርኒያ ግዛት ሴናተር እና የቀድሞ የግዛቱ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የነበሩት ካማላ ሀሪስ በአሜሪካ እየተካሄ ካለው የጥቁሮች ተቃውሞ ጋር ተያይዞ በሀገሪቱ ፖሊስ ለውጥ እንዲደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

ጆ ባይደን ዕጩ ፕሬዚዳንቷ ካማላ ሃሪስ በኢኮኖሚው እና በፖለቲካ በበቂ ሁኔታ ላልተወከሉት ያለፍርሃት ታጋይ እና አንደኛ ጠንካራ የህዝብ አገልጋይ ናቸው ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

የጀማይካ እና የህንድ የዘር ሀረግ ያላቸው ካማላ ሀሪስ በበኩላቸው በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ የምርጫ ፉክክር በጆ ባይደን ምክትል ዕጩ ፕሬዚዳንት ሆነው በመመረጣቸው ደስታቸውን በመግልፅ ጆ ባይደንን የ2020 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ አሸናፊ ለማድረግ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

በአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ፉክክር ታሪክ ሁለት ሴቶች ዕጩ ፕሬዚዳንት ሆነው ቀርበዋል።

አንደኛዋ ሳራ ፓሊን በ2008 ሪፐብሊካኖችን በመወከል ሲሆን ጌራልዲን ፌራሮ ደግሞ በ1984 ዴሞክራቶችን በመወከል በዕጩነት እንደቀረቡ መረጃዎች ያመለክታሉ።

በጆ ባይደን ዕጩ ፕሬዚዳንት በመሆን የተመረጡት ካማላ ከዶናልድ ትራምፕ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ጋር ጥቅምት ወር የገፅ ለገፅ ክርክር ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ነው የተነገረው።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.