Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በህገወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ 201 ቤቶችን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ እና ለአካል ጉዳተኛ ነዋሪዎች አስረከቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ  ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በህገወጥ መንገድ ተይዘው ከነበሩት 201 ቤቶችን በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ እና ለአካል ጉዳተኛ ነዋሪዎች አስረከቡ።

በቤቶቹ ርክክብ መርሐግብር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እንዳስታወቁት አዲስ አበባ ሀብታሙም ድሀውም በጋራ የሚኖሩባት ከተማ ናት ብለዋል።

በከተማዋ ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር በህገወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ ቤቶችን የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚያስፈልጋቸው እና ለችግር የተጋለጡ ነዋሪዎች በመለየት  በግልጽ እና በፍትሀዊነት እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።

ነዋሪዎች ህጋዊነት እንዲሰፍን እና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እንዲሁም የከተማዋ ሰላም ቀጣይነት እንዲኖረው የጀመረውን ተሳትፎ አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል ምክትል ከንቲባዋ።

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ይታያል ደጀኔ በበኩላቸው በክፍለ ከተማው  በህገወጥ መንገድ ከተያዙ 201 ቤቶችን በሁሉም ወረዳዎች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ እና አካል ጉዳተኛ ነዋሪዎች መሰጠቱን ተናግረዋል።

በቀጣይም በህገወጥ መንገድ የተያዙ ቤቶችን በማስለቀቅ ለችግረኛና አካል ጉዳተኛ ነዋሪዎች የሚሰጥ መሆኑን አቶ ይታያል መግለጻቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተርያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.