Fana: At a Speed of Life!

የህወሓት አመራሮች በትግራይ ህጻናት ላይ የጦር ወንጀል እየፈጸሙ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪው ህወሓት አመራሮች በትግራይ ህጻናት ላይ የጦር ወንጀል እየፈጸሙ መሆኑ ተገለፀ፡፡
ተገደው ወደ ውጊያው የገቡት ታዳጊዎች በዚህ ዘመን ፍትሃዊ ላልሆነ ጦርነት የዳረጓቸዉ አካሎች በህዝብ ላይ እየፈጸሙ ያሉት ተግባር የሚያሳፍር በመሆኑ የትግራይ ህዝብ ሊቃወማቸው ይገባል ብለዋል፡፡
የራሳቸውን ልጆች በተሻለ ሁኔታ እያኖሩ የደሃ ልጆችን ለሞት የሚዳርጉትን የአሸባሪው ህወሓት አመራሮች ህዝቡ መታገል አለበት በማለት ቁጭታቸውን የገለፁት ታዳጊዎቹ ትግራይ ተወራለች ነጻ ማውጣት አለብንም ነው ያሉት፡፡
በጦርነቱ በርካታ ታዳጊዎች ሲጎዱ ቀሪዎቹ የተሳካላቸው ደግሞ ማምለጥ መቻላቸውን የገለፀው ገብረሊባኖስ የማነ÷ እሱም በአፋር በኩል ተገደው በገቡበት ጦርነት ሲሸነፉ መሳሪያውን ጥሎ ለማምለጥ ሲሞክር መያዙንም ተናግሯል።
ተገዶ ወደ ጦርነቱ የገባው ታዳጊ ገብረ አርአያ ደግሞ ለውጊያ በቂ ስልጠና ሳይወስዱ የተወሰነ የመሳሪያ መፍታትና መግጠም ሒደትን ብቻ አይተው በአፋር ግንባር እንደተላኩ ተናግሯል፡፡
መሳሪያ ከቆሰሉ ሰዎች ወይም ከመከላከያ ነጥቀን እንሰጣችኋለን ተብለው በባዶ እጃቸው ወደ ጦርነቱ ሲገቡ ተደናግጦ ህይወቱን ለማዳን ሾልኮ ለማምለጥ ሲሞክር መያዙን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.