Fana: At a Speed of Life!

የሐረርና ድሬዳዋን የውሃ ችግር ለመቅረፍ ተጨማሪ ጉድጓዶችን መቆፈርና ከአጎራባች ክልሎች ጋር መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃ መገኛ ቦታዎችን ለይቶ ጉድጓዶችን በመቆፈር፣ ከአጎራባች ክልሎችና ከከተማ አስተዳደሮች ጋራ በመነጋገርና ተቀናጅቶ በመሥራት ለውሃ አቅርቦት ችግር እልባት መፈለግ አስፈላጊ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ ገለጹ፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከሐረርና ድሬዳዋ ከተሞች የውሃ አገልግሎት ሃላፊዎች ጋር በመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አቅርቦት ላይ ያተኮረ ውይይት በድሬዳዋ ከተማ አካሂደዋል፡፡

የስራ ሀላፊዎች በውሃ አገልግሎቶቹ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን÷ የከተሞቹ የውሃ አገልግሎት ሃላፊዎችም ያገጠሟቸውን ችግሮች ተናግረዋል፡፡

በተለይም ከኃይል መቆራረጥ፣ ከውሃ ጉድጎዶች የውሃ መጠን መቀነስ፣ የካልሲየም ካርቦኔትና ሌሎች ችግሮች ጋር በተያያዘ በሁለቱም ከተሞች ለሕብረተሰቡ በሚፈልገው ደረጃ በቂ ውሃ ማቅረብ እንዳልተቻለ ገልጸዋል፡፡

የከተሞቹ አገልግሎቶች ችግሩን ለመፍታት የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅድ አዘጋጅተው መሥራት እንዳለባቸውም ዶክተር ኢንጅነር ሀብታሙ መጠቆማቸውን ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የውሃ መገኛ ቦታዎችን ለይቶ ተጨማሪ ጉድጓዶችን መቆፈር፣ ከአጎራባች ክልሎችና ከከተማ አስተዳደሮች ጋራ በመነጋገርና ተቀናጅቶ በመሥራት ለችግሮቹ እልባት መፈለግ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ሚኒሰትሩ ግለጸዋል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.