Fana: At a Speed of Life!

የቀድሞው የፈረንሣይ ፕሬዚደንት ሳርኮዚ እስራት ተፈረደባቸው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ኒኮላ ሳርኮዚ በ2012 በተካሄደው ያልተሳካ የምርጫ ዘመቻ በህገወጥ መንገድ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸው በመረጋገጡ የአንድ ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል።

ጉዳያቸው በፓሪስ ፍርድ ቤት የታየው የ66 ዓመቱ ኒኮላ ሳርኮዚ፥ በህግ ከተፈቀደው ውጭ በአስር ሚሊየኖች የሚቆጠር ዩሮ ተጨማሪ ወጪ በማውጣታቸው ቅጣቱ ተወስኖባቸዋል።

በዚህ ድርጊት ከፕሬዚደንቱ ጋር በመተባበራቸው ክስ የተመሰረተባቸው 13ቱም ተከሳሾች ጥፋተኛ ተብለዋል።

ሳርኮዚ ፍርድ ቤት ቀርበዉ ጥፋተኛ ከተባሉ በኋላ የእስር ቅጣታቸዉ በቤታቸዉ ሆነው በብረት አጥር ግቢ ውስጥ የእስር ጊዜያቸውን ሊያሳልፉ እንደሚችሉ ዳኛው ተናግረዋል፡፡

ሆኖም ሳርኮዚ ጥፋተኛ አይደለሁም በማለት ይግባኝ ይጠይቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በአመለወርቅ ደምሰው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.