Fana: At a Speed of Life!

የአርቲስ ሐጫሉ ሁንዴሳን ስራዎች የሚዘክር ስነ ስርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአርቲስ  ሐጫሉ ሁንዴሳን ስራዎች የሚዘክር ስነ ስርዓት በአዲስ አበባ ተካሄደ።

በሸራተን አዲስ ትላንት ምሽት በተካሄደው ስነ ስርዓት የሙያ አጋሮቹ የአርቲስቱን ስራዎች በማንሳት ለቤተሰቦቹ ያላቸውን አጋርነት አሳይተዋል።

አርቲስት አሊ ቢራን ጨምሮ የተለያዩ አርቲስቶች ሐጫሉ በጥበብ ስራዎቹ ለእኩልነት እና ለፍህት ያደረጋቸውን ተጋድሎችና የስራውን ጠንካራ መልዕክቶች በማንሳት ዘክረዋል።

ሐጫሉ ህይወቱ በግፍ ብታልፍምስራዎቹ ግን በአሮሞ እና በኢትዮጵያ ህዝቦች ልቦና አብሮ የሚቆይ መሆኑን አንስተዋል።

እንዲሁም የአርቲስቱን ዓላማ ዘላቂነት እንዲኖረው አድናቃዎቹ እና ህዝቡ ፈለጉን ተከትለው ለአንድነትና እኩልነት እንዲቆሙ ጥሪ ቀርቧል።

በዚሁ ስነ ስርዓት ላይ ለአርቲስቱ ዝክር የተዘጋጀ ህብረ ዜማም ለታዳሚያን ቀርቧል፡፡

በስነ ስርዓቱ ላይ የሙያ አጋሮቹ፤ ቤተሰቦቹ እና የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል።

 

በ አዳነች አበበ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.