Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ሃገራት የኮሮና ቫይረስ ክትባት እየተረከቡ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በርካታ የአፍሪካ ሃገራት የመጀመሪያቸው የሆነውን የኮሮና ቫይረስ ክትባት እየተረከቡ ነው፡፡

ክትባቱ ኮቫክስ በተሰኘው ዓለም አቀፍ ጥምረት አማካኝነት ነው ወደ ሃገራቱ እየተሰራጨ የሚገኘው፡፡

ከሃገራቱ መካከል ኬንያ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ናይጄሪያ፣ አንጎላና ጋምቢያ ይገኙበታል፡፡

ኬንያ ለ500 ሺህ ሰዎች የሚበቃ ከ1 ሚሊየን በላይ መጠን ያለው የአስትራዜኒካ ክትባት ተቀብላለች፡፡

ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ደግሞ 1 ነጥብ 7 ሚሊየን መጠን የያዘ ክትባትን ወስዳለች፡፡

በተጨማሪም እስከ ግንቦት መጨረሻ ድረስ 6 ነጥብ 9 ሚሊየን መጠን የያዘ ክትባት እንደምትረከብም ይጠበቃል፡፡

አንጎላ 624 ሺህ፣ ጋምቢያ 36 ሺህ መጠን የያዘ የአስትራዜኒካ ክትባት ተረክበዋል፡፡

በዓለም ጤና ድርጅት የተመሰረተው ኮቫክስ የተሰኘው ጥምረት ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ለ190 ሃገራት ከ2 ቢሊየን በላይ ክትባት ለማዳረስ እቅድ አለው፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.