Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አህጉራዊ የአመራር ክፍተቶችን ለመሙላት ይሰራል ተባለ

 

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ አህጉራዊ የአመራር ክህሎት ክፍተቶችን ለመሙላት የራሱን ድርሻ ለማበርከት እንደሚሰራ የአካዳሚው ፕሬዚደንት ዶክተር ምህረት ደበበ ገለጹ።

ዶክተር ምህረት እንደተናገሩት÷ አካዳሚው በአገሪቷና በአህጉሪቱ የአመራር ክፍተቶችን ለመሙላት የሚሰራ ተቋም ነው።

በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ መሰል የአመራር ክፍተቶች መኖራቸውን ጠቁመው አካዳሚው እነዚህን ችግሮች ለማቃለል የራሱን ድርሻ እንደሚወጣ ነው የተናገሩት።

ተቋሙ የመለስ አመራር አካዳሚ በነበረበት ጊዜ በአስተሳሰብ ለውጥና በስብዕና ልህቀት ላይ ትኩረት ማድረጉን ጠቁመው አሁን ግን ዘርፈ ብዙ ጉዳዮችን ይዳስሳል ብለዋል።

የአካዳሚው ፕሬዚዳንት ሆነው ተቋሙን ከተቀላቀሉ ጀምሮ ተልዕኮውን በብቃት እንዲወጣ የሚቻላቸውን ሁሉ ለማድረግ እየሰሩ መሆኑንም ገልጸዋል።

አካዳሚው ብቁ አመራር ለመፍጠር የሚያስችል ሁሉን አቀፍ የአመራር የሥልጠና ማዕቀፍ መሆኑን ገልጸው የተለያዩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ጭምር የሚጠቅም መሆኑን አስረድተዋል።

ከኢትዮጵያ ጀምሮ አፍሪካዊ ጉዳዮችን የሚዳስስ አህጉራዊ ተቋም መሆኑን በመግለጽ።

በዚህ እሳቤ መሰረት አዲስ የተሾሙ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የሕዝብ አገልጋይ መሪ መሆን የሚያስችላቸው የአመራር ክህሎት ሥልጠና ተሰጥቷቸዋል ብለዋል።

ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎቹ በአካዳሚው በነበራቸው ቆይታ ከአካላዊ እንቅስቃሴ ጀምሮ ሥነ-ልቦናቸውን የሚያነቃቁ ለሥራ ዝግጁ የሚያደርጋቸው ሥልጠና መውሰዳቸውንም ጠቁመዋል።

በአካዳሚው በነበራቸው አምስት የሥልጠና ቀናት ወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮችን ጨምሮ ዓለም አቀፋዊ ኩነቶች ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች መዳሰሳቸውን አንስተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ሥልጠናው ሲጠናቀቅ በአካል ተገኝተው ለሠልጣኞቹ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የሥራ አቅጣጫ መስጠታቸው ይታወሳል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.