Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እና አዘርባጃንን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር ያለመ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዘርባጃን ከኢትዮጵያ ጋር በንግድና ኢንቨስትመንት ያላትን ኢኮኖሚያዊ ትስስር የማጠናከር ፍላጎት እንዳላት የአዘርባጃን ሪፐብሊክ ኤምባሲ ኃላፊ ሩስላን ናሲቦቭ አስታወቁ፡፡

የንግድ ትስስርና የውጭ ንግድ ፕሮሞሽን ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ከአዘርባጃን ሪፐብሊክ ኤምባሲ ኃላፊ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱ ሚኒስትር ዴኤታው ÷ ኢትዮጵያ የወጪ ንግድን ለማሳለጥ፣ ለማስተዋወቅ እና ለማሳደግ በኢኮኖሚ ማሻሻያ ላይ መሆኗን ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያና አዘርባጃን በንግድ እና ኢንቨስትመንቶች ትብብር በማድረግ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ማጠናከር እንደሚችሉም አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ በግብርና፣ በማዕድን፣ በቱሪዝም ዘርፎች ትልቅ አቅም እንዳላት ገልጸው አዘርባጃን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት በተለይም በማዕድን፣ በዘይትና በጋዝ፣ በንግድ እና ኢንቨስትመንት እንድትሳተፍ ያበረታታል ነው ያሉት፡፡

ሩስላን ናሲቦቭ በበኩላቸው÷ የአዘርባጃን ኢኮኖሚ በነዳጅ እና ጋዝ ወጪ ንግድ ላይ የተመሰረተ መሆኑን እና ከኢትዮጵያ ጋር በንግድ እና ኢንቨስትመንቶች መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ለማጠናከር ያላቸውን ፍላጎት ገልፀዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.