Fana: At a Speed of Life!

የከተራ በዓል ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10፣ 2014 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የከተራ በዓል በዛሬው ዕለት በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ዘንድ በዛሬው እለት ተከበረ።
በአዲስ አበባ የከተራ በዓል ለመታደም የእምነቱ ተከታዮች ከየአድባራቱ የተወጣጡ ታቦታትን አጅበው ወደ ጃን ሜዳ ሄደዋል።
በተጨማሪም በከተራ በዓሉ ላይ የሀገረ ስብከት ሀላፊዎች፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ሀላፊዎች እና የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች ተገኝተዋል።
ታቦታቱ ከአድባራት ወጥተው በካህናት፣ በዲያቆናት ፣በመዘምራን እና በምዕመናን ታጅበው ነው ወደ ጥምቀተ ባህሩ አቅንተዋል።
በነገው እለት ደግሞ የጥምቀት በዓል በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስርዓቶች የሚከበር ይሆናል።
በዘንድሮ የከተራና የጥምቀት በዓል ላይ “ወደ ሀገር ቤት” ሀገራዊ ጥሪን ተቀብለው የመጡ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በብዛት የሚታደሙበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
የከተራና የጥምቀት በዓላት በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ከሚከበሩ ሃይማኖታዊና የአደባባይ በዓላት መካከል ይጠቀሳሉ።
በፌቨን ቢሻው
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፤ እንገንባ፤ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.