Fana: At a Speed of Life!

የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ትክክለኛ ፣ ወቅታዊና ፈጣን መረጃ ለኅብረተሰቡ ማድረስ ይጠበቅባቸዋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመረጃ ክፍተትን በመለየት ብስለት በተሞላበት ሁኔታ ለኅብረተሰቡ ወቅታዊና ፈጣን መረጃን ተደራሽ ማድረግ ከኮሙኒኬሽን ባለሙያ ይጠበቃል ተባለ፡፡
 
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ የኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የስልጠና ማዕከል ስልጠና እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡
 
ስልጠናው ብቃት፣ አቅም፣ ህዝባዊነትና ወገንተኝነትን መሰረት ያደረገ የኮሙኒኬሽን አመራርና ባለሙያን ለመፍጠር ያግዛል ተብሏል፡፡
 
የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ በምክትል ቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የህዝብ ግንኙነትና ስልጠና ኃላፊ አቶ ሁሴን ዝናብ፥ በከተማ አስተዳደሩ ከ400 በላይ የኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች በተለያዩ ዙሮች ስልጠናውን እንዲወስዱ ይደረጋል ብለዋል፡፡
 
ስልጠናው በኅበረተሰቡ ጥያቄና ቅሬታ ላይ ትኩረት ያደረገ ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎችን ማድረስ የሚያስችል፥ እንዲሁም አጋጣሚዎችን ተጠቅመው ህዝብን ለማወናበድ የሚጥሩ አካላትን መከላከል የሚችል የኮሙኒኬሽን መዋቅር ለመፍጠር እንደሚያግዝ ተናግረዋል።
 
ስልጠናው ለተከታታይ ሰባት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን፥ መሰረታዊ ተግባቦትብ ግንኙነት፣ እቅድ ዝግጅትና ትግበራ እንዲሁም ዜና ዝግጅት፣ ትንታኔና የሀተታ ጽሁፍ ዝግጅት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው ተብሏል፡፡
 
ስልጠናው የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮና በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የስልጠና ማዕከል በገቡት ውል መሰረት ነው እየተሰጠ የሚገኘው፡፡
 
 
በዘቢብ ተክላይ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.