Fana: At a Speed of Life!

የደንብ ማስከበር ባለስልጣን የ121 አቅመ ደካማና አረጋውያን ቤቶችን እድሳት አስጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በተያዘው ክረምት የ121 አቅመ ደካማና አረጋውያን ቤቶችን እድሳት ጀምሯል።

ባለስልጣኑ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የ121 ወገኖችን መኖሪያ ቤቶች ለማደስ ያቀደ ሲሆን÷ ስራውን በዛሬው ዕለት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስጀምሯል።

የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ÷የደንብ ጥሰትን ከመከላከል ባለፈ በክረምቱ በተለያዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ላይ እየተሳተፉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከባለስልጣኑ ሰራተኞች ባለሃብቶችና ሌሎችም የማህበረሰብ ክፍሎች በሚሠበሠብ  ገንዘብ በክረምቱ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የችግረኛ እና አቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት እድሳት ማስጀመሩን ገልጸዋል።

የቤት እድሳት መርሐ ግብሩ በአቃቂ  ቃሊቲ  ክፍለ ከተማ በወረዳ  9 እና 1 በዛሬው ዕለት በይፋ እንደተጀመረ መናገራቸውን  ኢዜአ ዘግቧል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደምብ ማስከበር ባለስልጣን ሰራተኞች በትናንትናው ዕለት በመስቀል አደባባይ የደም ልገሳ ማድርጋቸውም ተመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

 

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.