Fana: At a Speed of Life!

የድሬዳዋ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ለተፈናቃዮች ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ወገኖች ከ5 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የምግብና የአልባሳት ድጋፍ አድርጓል፡፡
 
ምክር ቤቱ ህዝበ ሙስሊሙን በማስተባበር በየመስጅዱ ያሰባሰብውን 50ኩንታል ሩዝ፣ 250 ካርቶን ቴምር፣ የምግብ ዘይትና ፓስታ እንዲሁም ከ500 ሺህ በላይ የሚያወጣ የብርድ ልብስ፣ የተለያዩ አልባሳትና ጫማዎችን ነው ድጋፍ ያደረገው፡፡
 
የድሬዳዋ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ፕሬዚዳንት ሼክ አብደላ መሐመድ÷ ለተጎዱ ወገኖች በተቻለ አቅም ድጋፍ ማድረግ ሃይማኖታዊ ግዴታ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
 
ምክር ቤቱ ባቀረበው ጥሪ መሰረት የድሬዳዋ ሙስሊሞች አፋጣኝ ምላሽ በመስጠታቸው አመስግነው ድጋፉ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
 
ድጋፉን የተረከቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ÷ምክር ቤቱ ድሬዳዋ የምትታወቅበትን የመፈቃቀር፣ የመቻቻልና በአብሮነት የቆየ እሴትን በተግባር ያሳየ አርአያነት ያለው ተግባር በማከናወኑ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
ህዝበ ሙስሊሙ እያደረገ ካለው ድጋፍ ባሻገር ከሌሎች ጋር በመሆኑ የአካባቢውን ሠላም በንቃት እንዲጠብቅም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
 
ምክር ቤት በጦርነቱ ምክንያት ከደሴና ኮምቦልቻ አካባቢዎች ተፈናቅለው ለሚገኙ ወገኖች ከህዝበ ሙስሊሙ አሰባስቦ ድጋፍ ያደረገው የምግብና የአልባሳት ድጋፍ በአጠቃላይ ከ5 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በቢቂላ አለሙ
 
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.