Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን አካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት 5ኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ዛሬ አካሂዷል።

ጉባኤው በነበረው የአንድ ቀን ቆይታ በክልሉ በየእርከኑ የሚገኙ የምክር ቤቱ አባላት የሕዝብ ተወካዮችን ብዛት ለመወሰን የወጣ ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አፅድቋል።

የጉባኤ አባላት በሰጡት አስተያየት በክልሉ የሚገኙ ብሄረሰቦች በፖለቲካው ዘርፍ እኩል ተሳታፊ እንዲሆኑ ከማድረግ አንፃር ረቂቅ አዋጁ ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት 156 መቀመጫዎች ያሉት ሲሆን የየብሄረሰቡ ተወካዮች በተቀመጠላቸው ወሰን መሰረት ላለፉት በርካታ አመታት ሲተዳደሩ ቆይተዋል።

የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ ጁል ናንጋል በጉባኤው መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት÷ በክልሉ ብሎም በአገር ደረጃ እየተስፋፋ የመጣውን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ጠንክሮ መሥራት ያስፈልጋል።

በተለይም የምክር ቤቱ አባላት እና በየደረጃው የሚገኘው አመራር የላቀ ሚና መጫወት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዘበዋል።

“ዘንድሮ የሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ እንዲከናወን ሁሉም አበከሮ ሊሠራ ይገባዋል” ብለዋል አቶ ጁል።

በክልሉ ያለውን ሰላም በማጠናከር የተጀመሩ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን ውጤታማ ለማደረግ መትጋት እንደሚገባም አመላክተዋል።

በአስቸኳይ ጉባኤው ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ የክልል ምክር ቤት የጉባኤ አባላት እንዲሁም የዞን፣ የወረዳና የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ተሳታፊ ነበሩ፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.