Fana: At a Speed of Life!

የጠላትን አስተሳሰብ ከሕዝብ የመነጠል ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል-አቶ አብርሃም አለኸኝ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠላትን አስተሳሰብ ከሕዝብ የመነጠል ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የፓለቲካና ርዕዮተ ዓለም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ ሚኒስትር አቶ አብርሃም አለኸኝ ገለጹ፡፡
 
አቶ አብርሃም የመልካም አስተዳዳር ችሮግችን ለመፍታት አመራሮች ተገልጋዮችን በቀጥታ የሚያገኙበት ቀናት መመቻቸቱ የሕዝብን ችግሮች ለማዳመጥና መፍታት ምቹ ሁኔታ የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
በአገልግሎት አሠጣጥ ላያ ሕዝቡ የሚያሳቸውን ችግሮችን በተጨባጭ እየፈታ እና ተጠቃሚ እያደረገ ከመሆን አንጻር በየጊዜው እየተገመገመ መሄድ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
 
በክልሎች መካከል ያለው የትብብርና የወንድማማችነት መንፈስ የሚስተዋሉ ችግሮችን በቀላሉ መፍታት ማስቻሉን የገለጹት ሀላፊው÷ ለአብነትም በአማራና በቤኒሻንጉል አዋሳኝ አካባቢዎች የሰላም እና ጸጥታ ማስተባበሪያ ማዕከል በመገንባት የተገኘው ውጤት ልምድ የሚወሰድበት ነው ብለዋል፡፡
 
ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ከመታገል አኳያ የፍትህ አስተባባሪ ኮሚቴ እና የድርጅት አስተባባሪ ኮሚቴዎች በመናበብና በአንድነት መስራት የሚነሱ የፍትህ ጥያቄዎች በተጨባጭ ለመፍታት ወሳኝ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
 
የአገራችን የብልጽግና ጉዞ እንቅፋት በሆኑት ሸኔ እና ህወሓት እንዲሁም በየአካባቢው በሕገ-ወጥ መንገድ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ቡድኖች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቁመው÷ ጠላት የሚንቀሳቀስበት አመቺ እድል እንዳይኖው ተከታታይ የሆነ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን መቀጠል እንዳለበት አንስተዋል፡፡
 
በ90 ቀናት እቅድ ከከተማ ግብርና አኳያ በአዲስ አበባ ከተማ የተሻለ አፈጻጸም ቢታይም በሌሎች ዘንድ ግን ጉድለት በመታየቱ መታረም እንዳለበት አመላክተዋል፡፡
 
የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት የፓለቲካና ርዕዮተ ዓለም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሳ አሕመድ በበኩላቸው÷ የጸጥታ ችግሮችን ለመፍታት ከሕዝብ ጋር በመሆን የተሰራው ስራ አበረታች መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
የአባላት ጥራትን ከማስጠበቅ አኳያ የሕዋሳትና መሰረታዊ አደረጃጀት በአቅም ግንባታን በማጠናከር ጎልተው እንዲወጡ ማድረግ ይገባል ማለታቸውን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አቶ ሙሳ አያይዘውም በሕዝብ ዘንድ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች በሕዝብ ዘንድ ያመጡት ለውጥ ዋናው መመዘኛ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
 
ዘርፉ ለሁለት ቀናት በአዳማ ከተማ ሲያካሂድ የነበረውን የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ያጠናቀቀ ሲሆን÷ የ2015 በጀት ዓመት እቅድን አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.