Fana: At a Speed of Life!

የፅንስ መቋረጥ ከፍተኛ ጭንቀትን ያስከትላል – ጥናት

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የፅንስ መጨናገፍ ለከፍተኛ ጭንቀት እንደሚዳርግ አንድ ጥናት አመላከተ።

በእንግሊዝ የተደረገው ጥናት በእርግዝና ወቅት ፅንስ መጨናገፍ ያጋጠማቸው ሴቶች ከአደጋው በኋላ ለረጅም ጊዜ ከፍተኛ ለሆነ ውጥረት እና ጭንቀት እንደሚጋለጡ አመላክቷል፡፡

በዚህ መልኩ የፅንስ መጨናገፍ ካጋጠማቸው ስድስት ሴቶች መካከልም አንደኛዋ ለከፍተኛ ጭንቀት እንደምትዳረግም ነው የጥናት ውጤቱ ያሳየው።

በ650 ሴቶች ላይ በተደረገ ጥናት 29 በመቶ የሚሆኑት ፅንሱ ከተቋረጠ በኋላ ባለው አንድ ወር ውስጥ ከፍተኛ ለሆነ ጭንቀት መዳረጋቸው ተመላክቷል።

ከዚህ ባለፈም ከ12 ሳምንት በፊት የፅንስ መጨንገፍ የሚያጋጥማቸውና ከማህፀን ውጭ እርግዝና ያጋጠማቸው እናቶች ለዚህ ችግር ይጠቃሉም ነው ያሉት ጥናቱን ያደረጉት ባለሙያዎች።

ከደረሰባቸው የፅንስ መጨናገፍ በኋላ አንድ ወር ውስጥ 24 በመቶ የሚሆኑት የጭንቀት ምልክቶች እና 11 በመቶ የድብርት ስሜት እንደነበራቸውም ተገልጿል።

እንደ ጥናቱ ከሆነ ይህ አሃዝ ከዘጠኝ ወራት በኋላ ወደ 17 በመቶ እና 6 በመቶ ቀንሷል።

የጥናት ቡድኑ አባላት ሴቶች ከፅንስ መጨንገፍ በኋላ የበለጠ ጥንቃቄ እና ልዩ እንክብካቤ ይፈልጋሉ ብለዋል።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.