Fana: At a Speed of Life!

ለ6 ዓመታት የሚተገበር ውጤታማ የጤና አመራር መርሐ ግብር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስቴር ለሚቀጥሉት ስድስት ዓመታት የሚተገበር ሀገር አቀፍ ውጤታማ የጤና አመራር መርሐ ግብር ዛሬ በይፋ አስጀምሯል።

የጤና ሚኒስቴር ዴዔታ ዶ/ር አየለ ተሾመ በመርሐ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ እንዳሉት፥ የጤናው ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ቢሆንም የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት ውጤታማ የጤና አመራር መገንባት አስፈላጊ ነው።

ለዚህም ውጤታማ የጤና አመራር መርሐ ግብር ትግበራ ከዚህ ዓመት ጀምሮ ለሚቀጥሉት ስድስት ዓመታት በስራ ላይ ይውላል ነው ያሉት።

የመርሐ ግብሩ ዓላማም ለጤናው መስክ ብቁ አመራርን መፍጠር፣ የሴቶችን እና የዘርፉ ተተኪ ወጣት አመራሮችን ተሳትፎና አቅም ማሳደግ መሆኑን ተናግረዋል።

በሀገሪቱ ያለውን ውስን ሃብት በመጠቀም የጤና ዘርፉን ለማሳደግ ውጤታማ አመራር መገንባት የግድ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴዔታው ፥ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎም ወሳኝ እንደሆነ ነው ያነሱት።

ባለፉት ጊዜያት የህክምና ስርዓቱ እየተሻሻለ ቢመጣም ሙያዊ ክፍፍሎች በመኖራቸው የቡድን ስራ እየቀነሰ መምጣቱ ተግዳሮት መፍጠሩን ጠቁመዋል፡፡

በመሆኑም ችግሩን ለመቅረፍ በስድስት ዓመቱ መርሐ ግብር በሙያው የሰለጠኑ እና የጤናውን ዘርፍ በጥራትና በብቃት የሚመሩ አመራሮችን ለመፍጠር ይሰራል ነው ያሉት ዶ/ር አየለ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.