Fana: At a Speed of Life!

የ12ኛ ክፍል ፈተናን ለመስጠት ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሠራ መሆኑን ቢሮው ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተናን በሠላማዊ መንገድ ለመስጠት ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለጸ፡፡
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተራዝሞ የነበረውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም ለመስጠት ዕቅድ ተይዟል ብሏል ቢሮው፡፡
የቢሮው የፕላን ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ቃሲም ኢብራሂም ፈተናውን በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች በሚገኙ 21 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ፈተናውን በሠላማዊ መንገድ ለመስጠት እንዲቻልም የንቅናቄ ሰነድ ተዘጋጅቶ በየደረጃው ከሚገኙ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እየተካሄደ ስለመሆኑም ጠቁመዋል፡፡
በክልሉ ወደ 3 ሺህ 150 የሚጠጉ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተናን ይወስዳሉ ብለዋል፡፡
ለፈተናው ስኬታማነት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡም ጥሪ ማቅረባቸውን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.