Fana: At a Speed of Life!

ደቡብ ሱዳን የሃገር ውስጥ በረራ አገልግሎት የሚሰጠውን አየር መንገድ አገደች

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ደቡብ ሱዳን አንድ አነስተኛ አውሮፕላን መከስከሱን ተከትሎ የሃገር አየር መንገዱን ማገዷ ተሰማ፡፡
የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር አውሮፕላኑ ማክሰኞ መከስከሱን ተከትሎ አየር መንገዱ በጊዜያዊነት በረራ እንዳያደርግ አግደዋል፡፡
አውሮፕላኑ ከተነሳ ከደቂቃዎች በኋላ በምስራቅ ጆንግሌ ግዛት መከስከሱ ነው የተሰማው፡፡
በዚህም ኬንያዊውን የአውሮፕላን አብራሪ ጨምሮ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ መንገደኞችና ሰራተኞች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ኪር በሰጡት መግለጫ የአየር መንገዱ መታገድ ጊዜያዊ እርምጃ ነው ብለዋል ፡፡
እርምጃው የሚደርሰውን የአውሮፕላን አደጋ ለመከላከልና ህዝባዊ አመኔታን ለማግኘት ያለመ ነው ተብሏል፡፡
የሃገር ውስጥ የበረራ አገልግሎት የሚሰጠው አየር መንገዱ በደቡብ ሱዳን ጠቅላላ የቢዝነስ ማህበረሰብ እና አሰሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ባለቤትነት የሚተዳደር ነው፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.