Fana: At a Speed of Life!

ጋቦን እና ቶጎ የጋራ ብልፅግና ሀገራት ስብስብን ለመቀላቀል ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት አገኘ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 20 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጋቦን እና ቶጎ የጋራ ብልፅግና ሀገራት ስብስብን ለመቀላቀል ያቀረቡት ጥያቄ ባሳለፍነው ቅዳሜ ተቀባይነት ማግኘቱ ተነግሯል፡፡
54 አባል ሀገራትን ያቀፈው የጋራ ብልፅግና ሀገራት ሁለቱን ሀገራት በተጨማሪ አባልነት የተቀበለው በሩዋንዳ ባካሄደው የጉባዔው የመዝጊያ ቀን ላይ ነው ተብሏል፡፡
የሩዋንዳው የጋራ ብልፅግና ሀገራት ጉባዔ ሲጠናቀቅ የሀገሪቷ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ ጋቦን እና ቶጎን በአባልነት እንደ ቤተሰብ መቀበላቸውን አስታውቀዋል፡፡
ሩዋንዳ በፈረንጆቹ 2009 የጋራ ብልፅግና ሀገራትን ከተቀላቀለች በኋላ ሁለቱ በአዲስ አባልነት የተቀላቀሉት የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹ ፈረንሳይኛ ተናጋሪ አዲስ አባላት መሆናቸውም ተነግሯል።
አብዛኛዎቹ የጋራ ብልፅግና አባል ሀገራት የቀድሞ የብሪታኒያ ቅኝ ግዛቶች እንደ መሆናቸው እንግሊዝኛ ተናጋሪዎች መሆናቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን በዘገባው አስታውሷል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.