Fana: At a Speed of Life!

ግሪክ የመጀመሪያ ሴት ፕሬዚዳንቷን መረጠች

አዲስ አበባ ፣ ጥር 13 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ግሪክ የመጀመሪያዋን ሴት ፕሬዚዳንት መረጠች።

አዲሷ ተመራጭ ፕሮኮፒስ ፓቮሎፖሎስን በመተካት የፊታችን መጋቢት ወር ስልጣን ይረከባሉ።

ተመራጯ ፕሬዚዳንት የፓርላማውን አብላጫ ድምጽ በማግኘት የሃገሪቱ ርዕሰ ብሄር ሆነዋል።

ግለሰቧ ከዚህ ቀደም በሃገሪቱ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ዳኛ በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

ከዚህ ባለፈም ከአየር ንብረት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች በዳኝነት ያገለገሉ ሲሆን፥ በአየር ንብረት ለውጥ በርካታ ጽሁፎችንም አዘጋጅተዋል።

ምንጭ፦ አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.