Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የኮይሻ የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የኮይሻ የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን ጎበኙ።

በኦሞ ወንዝ ላይ እየተገነባ የሚገኘው ይህ የኤሌከትሪክ ኃይል ማመንጫ ግንባታው 37 በመቶ መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመልክተዋል።

ፕሮጀክቱ በከፍተኛ ሁኔታ ተጓትቶ የቆየ እንደነበርና በቅርቡ ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ነው የገለፁት።

በዓመት የ6 ሺህ 400 ጊጋዋት አወርስ መጠን ያለው ኃይል እንደሚያመነጭ ይጠበቃል።

እስካሁን ለ4 ሺህ ያህል ሰዎች የሥራ ዕድል ያስገኘ ሲሆን፥ ፕሮጀክቱ ግንባታው ሲቀጥል ለተጨማሪ ሰዎች ሥራን ይፈጥራል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ግድቡ ከአዲሱ የኮይሻ ፕሮጀክት ጋር ተዳምሮ አካባቢውን ወደ ልህቀት ያደርሳልም ነው ያሉት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.