Fana: At a Speed of Life!

ጨፌ የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጨፌ ኦሮሚያ የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ።
ጨፌው የ158 ዳኞችን ሹመት አጽድቋል።
በተጨማሪም አቶ ነመራ ቡሊ የኦሮሚያ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ሀላፊ፥ አቶ ጌቱ ወዬሳ የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ሀላፊ፥ አቶ ሁሴን ኡስማን የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ፥ ወ/ሮ ሰይዳ ኡስማን የክልሉ ሴቶች፥ ህጻናትና ወጣቶች ቢሮ ሀላፊ በመሆን ተሹመዋል።
አቶ አብዱልሀኪም አብደላ የጨፌ ኦሮሚያ የገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነው እንዲያገለግሉ ለጨፌው ቀርቦ ጸድቋል።
ጨፌ ኦሮሚያ በ5ኛ የስራ ዘመን 6ኛ አመት 13ኛ መደበኛ ስብሰባው የ2013 ዓ.ም የግማሽ አመት የስራ አፈፃፀምን የገመገመ ሲሆን ዛሬ በሁለተኛ ቀን ውሎው የተለያዩ አዋጆች ላይ በመወያየት አጽድቋል።
የኦሮሚያ የቤቶች ልማት አስተዳደርና ማስተላለፍ፣ ኤክሳይዝ ታክስ፣ የውሀ ኃብት ልማት፣ የግብርና ምርት ጥራት ቁጥጥር፣ ስታቲስቲክስ፣ የመአድን ኃብት ልማት እና የክልሉን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለማሻሻል የተዘጋጁ ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.