Fana: At a Speed of Life!

10ኛው አገር አቀፍ የቱሪዝም ጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ በሠመራ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 10ኛው አገር አቀፍ የቱሪዝም ጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ “ቱሪዝም ለስራ-እድል ፈጠራ” በሚል መሪ ሀሳብ በሠመራ ከተማ ተካሂዷል፡፡
 
ኮንፈረንሱ በኢትዮጵያ ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዮት ከአፋር ባህልና ቱሪዝም ቢሮና ሠመራ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባባር ነው የተዘጋጀው፡፡
 
አላማውም የክልሉን ዘርፈ-ብዙ የቱሪዝም ሃብት ማስተዋወቅና በጦርነትና ኮሮና ወረርሽኝ የተቀዛቀዘውን የጎብኚዎችን ፍሰት ለማነቃቃት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
 
በመድረኩም “ቱሪዝም በስራ እድል ፈጠራ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽና የአፋር ክልል ቱሪዝም ተጨባጭ ሁኔታ ፈተናዎችና መልካም አጋጣሚዎች” በሚል ጥናታዊ ጽሁፎች ለውይይት እንደሚቀርቡ ይጠበቃል።
 
በመድረኩ ላይ የቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር አመራሮች የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲቲዩት አመራሮች እንዲሁም የክልሉ ባህልና ቱሩዝም ሃላፊና የሰመራ ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.